ቀን 7/2/2009 ዓ.ም

የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ ቁጥር 10/2009

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ላብ ቴክኒሻኖች ለመቅጠር በ17/11/2008 ዓ.ም ባወጣው ማስታወቂያ የተመዘገቡ እና ለፈተና የተጠሩ እጩ ተወዳዳሪዎች የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ

Machine-shop BSC( የላብ ቴክኒሻኖች )

የፈተና ቀን 10/2/2009 ሰአት ከጠዋቱ 4:00  ቦታ ወልቂጤዩኒቨርሲቲዋናውግቢ

ተ.ቁ

ፈተና የተመለመለ እጩ ተወዳዳሪ ስም

ፆታ

የት/ት ዓይነት

ደረጃ

1

ሰለሞን ደምሴ

 

 

የመጀመሪያ ዲግሪ

አንተነህ አንዱአለም

 

 

የመጀመሪያ ዲግሪ

ቴዉድሮስ ስሜነህ

 

 

የመጀመሪያ ዲግሪ

መገርሳ ኡርጌቻ

 

 

የመጀመሪያ ዲግሪ

ብሌን አድማሱ

 

 

የመጀመሪያ ዲግሪ

6    

መሀሙድ አልካድር

 

 

የመጀመሪያ ዲግሪ

7    

አምርያ ከድር

 

 

የመጀመሪያ ዲግሪ

8

ጨመዳ ረጋሳ

 

 

የመጀመሪያ ዲግሪ

Machining ( የላብ ቴክኒሻኖች )

ለወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የ2009 ዓ.ም የትምህርተ ዘመን አዲስ ገቢ ተማሪዎች በሙሉ(New)

 በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ለ2009 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በመደበኛ ዲግሪ መርሀ-ግብር በትምህርት ሚኒስቴር መስፈርት መሰረት የተመደባችሁ አዲስ ተማሪዎች ምዝገባ ከመስከረም 26 እስከ 27/2009 ዓ.ም የነበረው ወደ ጥቅምት 7 እና 8/2009 ዓ.ም የተዛወረ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

  • የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ውጤት ዋናውንና ፎቶ ኮፒ
  • ብርድልብስ
  •  አንሶላ
  •  ስምንት ጉርድ ፎቶግራፍ ይዛችሁ መምጣት ይኖርባችኋል፡፡

ማስታወሻ፡

ከተገለፀው ቀን በፊትም ሆነ በኋላ ለሚመጡ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲው ምንም አይነት አገልግሎት አይሰጥም

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ

ለጥበብ እንተጋለን!!! 

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች በትምህርት ጥራት እና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያካሄዱት የስምንት ቀን ውይይት በፍፁም መግባባት እና መማማር ተጠናቀቀ፡፡

በውይይቱ በርካታ ሀገራዊ እና ተቋማዊ ጉዳዮች የተነሱ ሲሆን የሀይል መድረኮቹን በመሩት የዩኒቨርሲቲው ቦርድ ተወካዮች እና ከፍተኛ አመራሮች ተጨባጭ ምላሾች ከስምምነት ተደርሷል፡፡ አንዳንድ በማህበራዊ ድረገፆች የተገኙ ነገር ግን ተጨባጭነት የሌላቸው መረጃዎችን መሰረት በማድረግ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶችም ተሳታፊዎች እራሳቸው እና የቡድን ውይይትን የመሩ የጉራጌ ዞን አመራሮች፣ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ አመራሮች እና የዩኒቨርሲቲው መካከለኛ አመራሮች አጥጋቢ መልስ በመስጠት በጋራ ስምምነት ውይይቱ ሊጠናቀቅ ችሏል፡፡

ፅ/ቤታችን ያነጋራቸው ተሳታፊ መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞችም ሀገራዊ ስምምነት በሰላም እና በመከባበር ለመኖር ብቻ ሳይሆን ለዘላቂ የትምህርት ጥራትም አይነተኛ ፋይዳ እንዳለው እና በቀጣይም ይህንኑ መሰረት በማድረግ ለዩኒቨርሲቲው ልህቀት እና ለሀገሪቱ መሰረት ያለው ዘላቂ እድገት መረጋገጥ እጅ እና ጓንት ሆነው እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል፡፡ በውይይቱም በወሬ ደረጃ ሀገርን እና ሰላማዊ ህዝብን የሚያሸብሩ አሉባልታዎችን በመለየት ካሁን ቀደም በሌሎች የሀገራችን ክፍሎች የተነሱት አለመግባባቶች እና ቅሬታዎች ትክክለኛ ምንጭ እና ያሉበትን ደረጃ መረዳት ችለናል ብለዋል፡፡

ተሳታፊዎቹ በውጪ አፍራሽ ሀይሎች በሀገሪቱ ላይ የተቃጣውን የማጥፋት እና የማሸበር ዘመቻ አበክረው እንደሚቃወሙ ገልፀው ሀገሪቱ በምትወስደው ማንኛውም አይነት የህዝቡን ደህንነት እና ሰላም እንዲሁም የተጀመረውን አበረታች ልማት በሚያስቀጥሉ እርምጃዎች ላይ በቀጥታ ተሳታፊ እንደሚሆኑ አረጋግጠዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው አመራሮች በበኩላቸውም የመድረኩ ድባብ ለዩኒቨርሲቲውም ሆነ ለገዢው ፓርቲ እጅግ ጠቃሚ የሆኑ ምሁራዊ ግብአቶችን በአማራጭነት ያቀረበና ሁሉም ተሳታፊ በፍፁም ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የመሰለውን ተናግሮ አጥጋቢ ምላሽ ያገኘበት ነው ብለዋል፡፡

አመራሮቹ አክለውም እንዲህ አይነት መድረኮች ጠቀሜታቸው የጎላ በመሆኑ በዩኒቨርሲቲው የስራ ሂደት ውስጥ በእቅድ ተካተው በተደጋጋሚ የሚካሔዱና ሁሉም የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በእኔነት ስሜት የተሻሉ ሀሳቦችን እያቀረበ የትምህርት ጥራትን የሚያረጋግጥባቸው መድረኮች ይሆናሉ ብለዋል፡፡

ከተሳታፊዎች ለተነሱ የዩኒቨርሲቲው የአሰራር ላይ ቅሬታዎችም አፋጣኝ ምላሽ እንደሚሰጡ አረጋግጠዋል፡፡

ለጥበብ እንተጋለን

የሕዝብ እና አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር

 

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዙሪያ ውይይት አካሄዱ

በያዝነው መስከረም ወር ከ900 በላይ የሆኑ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና አስተዳደር ሰራተኞች በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዙሪያ ውይይት አካሄደዋል፡፡ውይይቱም በዩኒቨ ሲቲው የቦርድ ሰብሳቢ የተከፈተ ሲሆን በዩኒቨርሲቲው አመራሮች አወያይነትም ተካሄዷል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የቦርድ ሰብሳቢ አቶ መኩሪያ ሀይሌም ይህ የሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውይይት መድረክ መፈጠሩ ሀገራችን በምታደርገው የቴክኖሎጂ ሽግግር ለሚያስፈልጋት  የሰው ሀይል አቅርቦት ፡በብቃትና በጥራት ለማፍራት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአንበሳውን ድርሻ ከመውሰዳቸው የተነሳ ውይይቱ መካሄዱ ያለው ሚና ከፍተኛ ነው ሲሉ በአትኩሮት እንዲሳተፉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በውይይቱ ወቅት በአለፉት የመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ አመታት ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን የዳሰሱ ሲሆን በቀጣዩም የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ እንዳይደገሙ መወሰድ ስላለባቸው የመፍትሄ አቅጣጫዎች ተወያይተዋል፡፡

ሰነዱ ሀገራዊ ጉዳዮችን መዳሰሱ የኔነት ስሜት እንዲኖራቸውና ሀገራችን የምትከተለውን ፖሊሲ እንድናውቅ ረድቶናል ሲሉ በለውጥ ሰራዊት ግንባታ መሳሪያዎች አጠቃቀም ላይ የነበሩ ተግዳሮቶችን በመረዳት አሁን በያዝነው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን እንዴት መራመድ እንደሚቻል አቅጣጫዎች በማስቀመጡ ጥሩ እውቀት እና ግንዛቤ እንዳስጨበጣቸው የውይይቱ ተሳታፊዎች ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻም የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደር ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ መሀመድ አህመዲን ለሀገራችን ዘላቂ ልማት ለማስቀጠልና የጀመርነውን የእድገት እና የትራንስፎርሜሽ እቅድ በስኬት ለማጠናቀቅ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት  ባለድርሻ አካል እንደመሆናችን መጠን  ሃላፊነታችንን በትኩረት ልንወጣ ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

  ‹የህዝብ እና አለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት›

 

 

 

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ለ2008 ዓ.ም የት/ት ዘመን ተማሪዎች እየተቀበለ ይገኛል

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በ2008 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በ33 የትምህርት ክፍሎች የሚያስተምራቸውን ከ5500 በላይ ነባር ተማሪዎች ከመስከረም 18/2008 ዓ.ም ጀምሮ እጅግ በተቀናጀ የመስተንግዶ እና የምዝገባ ስርዓት እየተቀበለ ነው፡

በማግባት ላይ የሚገኙት ተማሪዎችም በዚህ ዓመት ዩኒቨርሲቲው በተሻለ የመነቃቃት መንፈስ እንደተቀበላቸው ገልፀው የትምህርት ዘመኑ በጋራ ጥረት ላይ በተመሰረተ መልካም ውጤት እንደሚጠናቀቅ ያላቸውን እምነት መግለፃቸውን የዘገበው የዩኒቨርሲቲው የህዝብ እና አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ነው፡፡

ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

 

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ለ2006 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሚከተሉት የትምህርት ዘርፎች በማታ (Extension) እና በሳምንቱ መጨረሻ (week end) መርሃ ግብር በመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በሚሰጠው ተከታታይ ትምህርት ምዝገባ ተማሪዎች ሲመጡ ማሟላት ያለባቸው

 

ለወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ነባር ተማሪዎች በሙሉ

2006.ም የነባር ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ጥቅምት 7 እና 8

Contact

Tamru Demsis (Ph.D)
Ac/V/President
Wolkite University, 07
Wolkite, 07
Ethiopia
+251 11 3220054
Mobile: 0930289749
This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

Contact

Abel Dula
Dean, College of Business and Economics
Wolkite, 07
Ethiopia
Mobile: +251912027866
This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
Scroll to top