በወልቂጤ ዪኒቨርሲቲ ውስጥ ባሉ የተማሪዎች ክበባትና ማህበራት መካከል የሚካሄደው ዓመታዊ የእስፖርት ውድድር ከህዳር 2/2010 ዓ.ም ጀምሮ በዪኒቨርሲቲው ሁለገብ ስታዲየም መካሄድ ጀመረ፡፡

የዩኒቨርሲቲው ስፖርትና መዝናኛ ሃላፊ አቶ ስራጅ ኑርበገን እንደተናገሩት ውድድሩ በተማሪዎች መካከል መቀራረብንና አንድነትን ከመፍጠሩ ባሻገር በ2010 ዓ.ም በጅማ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት ለሚካሄደው አገር አቀፍ የከፍተኛ ት/ት ተቋማት የስፖርት ውድድር ዩኒቨርሲቲውን የሚወክሉ ብቁ ስፖርተኞችን ለመመልመል ያግዛል፡፡

በወንዶች እግር ኳስ በጥሎ ማለፍ በቀዳሚነት የተገናኙት ወ/ጤ ክላስተር ማህበር ከሊቭ ፎር ጄኔሬሽን ክበብ ጋር ሲሆን በመደበኛ የጨዋታ ጊዜ ባዶ ለባዶ በመለያየታቸው በፍፁም ቅጣት ምት ወልቂጤ ክላስተር ማህበር ሊቭ ፎር ጄኔሬሽን ክበብን 7ለ6 በሆነ ውጤት አሸንፎ ለቀጣይ ዙር ማለፉን አረጋግጧል፡፡

እሁድ ህዳር 3/2010 ዓ.ም በተካሄደው የወንዶች እግር ኳስ ጨዋታ አኒማል ፕሮዳክሽን ማህበር ሜካኒካል ማህበርን 4ለ1 ሲቪል ኢንጂነሪግ ማህበር አርክቴክቸር ማህበርን 5ለ0 እንዲሁም ሰላም ፎረም ሳይንስና ቴክኖሎጂ ማህበርን 4ለ3 በማሸነፍ ወደ ቀጣይ ዙር ማለፋቸውን ያረጋገጡ ሌሎች ቡድኖች ሆነዋል፡፡

ውድድሩ በቀጣይ ቅዳሜ ህዳር 9/2010 ዓ.ም ፆታዊ ትንኮሳ ክበብ ከኮተም ማህበር ከጠዋቱ 2፡30 ኢንቫይሮሜንታል ማህበር ከተማሪዎች ህብረት በ5፡00 ሰዓት በሚያደርጉት ጨዋታ የሚቀጥል ሲሆን እሁድ ህዳር 10/2010 ዓ.ም ደግሞ በሁለተኛው የውድድር ዙር ወልቂጤ ክላስተር ማህበር ከአኒማል ፕሮዳክሽን ማህበር በ2፡30 ሰዓት እና ሲቪል ማህበር ከኤሌክቲሪካል ማህበር በ5፡00 ሰዓት ጨዋታዎችን ያካሂዳሉ፡፡

ለሁለት ሳምንታት በወንዶች የእግር ኳስ ውድድር ብቻ መርሀ-ግብሩን እያከናወነ ያለው ውድድር በቀጣይ ሳምንት የሴቶች እግር ኳስ ጨምሮ በሁለቱም ፆታዎች የመረብ ኳስ የእጅ ኳስ የማርሻል አርት፣ የቅርጫት ኳስ እና የጠረጴዛ ቴኒስ ውድድር እንደሚጀምሩ የነገሩን ደግሞ ከውድድሩ አስተባባሪዎች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ መሳይ ማርቆስ ናቸው፡፡

የስፖርት ውድድሩ እስከ ህዳር 30 /2010 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን ከ500 በላይ ተማሪዎችን እንደሚያሳትፍ የዘገበው የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ነው፡፡

 

Whos is online

We have 84 guests and no members online

Vacancy

Call for Papers

Contact

Tamru Demsis (Ph.D)
Ac/V/President
Wolkite University, 07
Wolkite, 07
Ethiopia
+251 11 3220054
Mobile: 0930289749
This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
Scroll to top