ቀን 7/2/2009 ዓ.ም

የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ ቁጥር 10/2009

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ላብ ቴክኒሻኖች ለመቅጠር በ17/11/2008 ዓ.ም ባወጣው ማስታወቂያ የተመዘገቡ እና ለፈተና የተጠሩ እጩ ተወዳዳሪዎች የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ

Machine-shop BSC( የላብ ቴክኒሻኖች )

የፈተና ቀን 10/2/2009 ሰአት ከጠዋቱ 4:00  ቦታ ወልቂጤዩኒቨርሲቲዋናውግቢ

ተ.ቁ

ፈተና የተመለመለ እጩ ተወዳዳሪ ስም

ፆታ

የት/ት ዓይነት

ደረጃ

1

ሰለሞን ደምሴ

 

 

የመጀመሪያ ዲግሪ

አንተነህ አንዱአለም

 

 

የመጀመሪያ ዲግሪ

ቴዉድሮስ ስሜነህ

 

 

የመጀመሪያ ዲግሪ

መገርሳ ኡርጌቻ

 

 

የመጀመሪያ ዲግሪ

ብሌን አድማሱ

 

 

የመጀመሪያ ዲግሪ

6    

መሀሙድ አልካድር

 

 

የመጀመሪያ ዲግሪ

7    

አምርያ ከድር

 

 

የመጀመሪያ ዲግሪ

8

ጨመዳ ረጋሳ

 

 

የመጀመሪያ ዲግሪ

Machining ( የላብ ቴክኒሻኖች )

ለወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የ2009 ዓ.ም የትምህርተ ዘመን አዲስ ገቢ ተማሪዎች በሙሉ(New)

 በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ለ2009 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በመደበኛ ዲግሪ መርሀ-ግብር በትምህርት ሚኒስቴር መስፈርት መሰረት የተመደባችሁ አዲስ ተማሪዎች ምዝገባ ከመስከረም 26 እስከ 27/2009 ዓ.ም የነበረው ወደ ጥቅምት 7 እና 8/2009 ዓ.ም የተዛወረ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

  • የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ውጤት ዋናውንና ፎቶ ኮፒ
  • ብርድልብስ
  •  አንሶላ
  •  ስምንት ጉርድ ፎቶግራፍ ይዛችሁ መምጣት ይኖርባችኋል፡፡

ማስታወሻ፡

ከተገለፀው ቀን በፊትም ሆነ በኋላ ለሚመጡ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲው ምንም አይነት አገልግሎት አይሰጥም

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ

ለጥበብ እንተጋለን!!! 

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች በትምህርት ጥራት እና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያካሄዱት የስምንት ቀን ውይይት በፍፁም መግባባት እና መማማር ተጠናቀቀ፡፡

በውይይቱ በርካታ ሀገራዊ እና ተቋማዊ ጉዳዮች የተነሱ ሲሆን የሀይል መድረኮቹን በመሩት የዩኒቨርሲቲው ቦርድ ተወካዮች እና ከፍተኛ አመራሮች ተጨባጭ ምላሾች ከስምምነት ተደርሷል፡፡ አንዳንድ በማህበራዊ ድረገፆች የተገኙ ነገር ግን ተጨባጭነት የሌላቸው መረጃዎችን መሰረት በማድረግ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶችም ተሳታፊዎች እራሳቸው እና የቡድን ውይይትን የመሩ የጉራጌ ዞን አመራሮች፣ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ አመራሮች እና የዩኒቨርሲቲው መካከለኛ አመራሮች አጥጋቢ መልስ በመስጠት በጋራ ስምምነት ውይይቱ ሊጠናቀቅ ችሏል፡፡

ፅ/ቤታችን ያነጋራቸው ተሳታፊ መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞችም ሀገራዊ ስምምነት በሰላም እና በመከባበር ለመኖር ብቻ ሳይሆን ለዘላቂ የትምህርት ጥራትም አይነተኛ ፋይዳ እንዳለው እና በቀጣይም ይህንኑ መሰረት በማድረግ ለዩኒቨርሲቲው ልህቀት እና ለሀገሪቱ መሰረት ያለው ዘላቂ እድገት መረጋገጥ እጅ እና ጓንት ሆነው እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል፡፡ በውይይቱም በወሬ ደረጃ ሀገርን እና ሰላማዊ ህዝብን የሚያሸብሩ አሉባልታዎችን በመለየት ካሁን ቀደም በሌሎች የሀገራችን ክፍሎች የተነሱት አለመግባባቶች እና ቅሬታዎች ትክክለኛ ምንጭ እና ያሉበትን ደረጃ መረዳት ችለናል ብለዋል፡፡

ተሳታፊዎቹ በውጪ አፍራሽ ሀይሎች በሀገሪቱ ላይ የተቃጣውን የማጥፋት እና የማሸበር ዘመቻ አበክረው እንደሚቃወሙ ገልፀው ሀገሪቱ በምትወስደው ማንኛውም አይነት የህዝቡን ደህንነት እና ሰላም እንዲሁም የተጀመረውን አበረታች ልማት በሚያስቀጥሉ እርምጃዎች ላይ በቀጥታ ተሳታፊ እንደሚሆኑ አረጋግጠዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው አመራሮች በበኩላቸውም የመድረኩ ድባብ ለዩኒቨርሲቲውም ሆነ ለገዢው ፓርቲ እጅግ ጠቃሚ የሆኑ ምሁራዊ ግብአቶችን በአማራጭነት ያቀረበና ሁሉም ተሳታፊ በፍፁም ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የመሰለውን ተናግሮ አጥጋቢ ምላሽ ያገኘበት ነው ብለዋል፡፡

አመራሮቹ አክለውም እንዲህ አይነት መድረኮች ጠቀሜታቸው የጎላ በመሆኑ በዩኒቨርሲቲው የስራ ሂደት ውስጥ በእቅድ ተካተው በተደጋጋሚ የሚካሔዱና ሁሉም የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በእኔነት ስሜት የተሻሉ ሀሳቦችን እያቀረበ የትምህርት ጥራትን የሚያረጋግጥባቸው መድረኮች ይሆናሉ ብለዋል፡፡

ከተሳታፊዎች ለተነሱ የዩኒቨርሲቲው የአሰራር ላይ ቅሬታዎችም አፋጣኝ ምላሽ እንደሚሰጡ አረጋግጠዋል፡፡

ለጥበብ እንተጋለን

የሕዝብ እና አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር

 

Whos is online

We have 91 guests and no members online

Call for Papers

Scroll to top