የካይዘን ስራ አመራር ፍልስፍናን በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መተግበሩ ውጤታማ እና ጥራት ያለው የሠው ሃይል ለማፍራት በሚደረገው ጥረት የማይተካ ሚና እንዳለው ተገለፀ፡፡

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ካይዘን ኢንስትቲዩት ጋር በመተባበር ‹‹የካይዘን አመራር ፍልስፍናን በመተግበር የዩኒቨርሲቲያችንን ተልዕኮ እናሳካልን›› በሚል መሪ ቃል የካይዘን ስራ አመራር ፍልስፍና የትግበራ እወጃ አካሂዷል፡፡

በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የካይዘን ስራ አመራር ፍልስፍናን መተግበሩ ተቋማቶቹ ከሚያጋጥማቸው የሠው ሃይል፣ የመዋለ-ንዋይና የአሠራር ብክነት ተላቀው ጥራቱን የጠበቀና የተሳለጠ የመማር ማስተማር ተግባር ለማከናወን እና ቀልጣፋና ውጤታማ የማህበረሰብ አገልግሎት ለመስጠት እንዲሁም በየተቋማቱ የሚከናወኑ የጥናትና ምርምር ስራዎች ችግር ፈቺ እና ለማህበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ እንደሚያግዝ ተገልጿል፡፡

    ‹‹የህዝብ እና አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት›› 

ÐÐ

ÐÐየተማሪዎችን ውጤትና ስነ-ምግባር ለማሻሻል የትምህርት ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ ተገለፀ፡፡

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ሳይንስ እና ስነ-ሰብ ኮሌጅ በስሩ በሚገኙ 6 የትምህርት ክፍሎች በ2009 የትምህርት ዘመን የላቀ ውጤት ላስመዘገቡና በትምህርት ልማት ሠራዊት ግንባታ የተሻለ አፈፃፀም ላሳዩ ተማሪዎችና መምህራን ማክሰኞ ግንቦት 15/2009 ዓ.ም የእውቅናና የማበረታቻ ሽልማት አበረከተ፡፡

በዕለቱ እውቅና የተሰጣቸው ተማሪዎችም ሽልማቱ በቀጣይ የትምህርት ቆይታቸው ከዚህ የተሻለ ለመስራት እንደሚያነሳሳቸው ተናግረዋል፡፡

            የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

ÐÐÐየተማሪዎችን ውጤትና ስነ-ምግባር ለማሻሻል የትምህርት ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ ተገለፀ፡፡

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ሳይንስ እና ስነ-ሰብ ኮሌጅ በስሩ በሚገኙ 6 የትምህርት ክፍሎች በ2009 የትምህርት ዘመን የላቀ ውጤት ላስመዘገቡና በትምህርት ልማት ሠራዊት ግንባታ የተሻለ አፈፃፀም ላሳዩ ተማሪዎችና መምህራን ማክሰኞ ግንቦት 15/2009 ዓ.ም የእውቅናና የማበረታቻ ሽልማት አበረከተ፡፡

በዕለቱ እውቅና የተሰጣቸው ተማሪዎችም ሽልማቱ በቀጣይ የትምህርት ቆይታቸው ከዚህ የተሻለ ለመስራት እንደሚያነሳሳቸው ተናግረዋል፡፡

            የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

Whos is online

We have 90 guests and no members online

Call for Papers

Scroll to top