• Registration

     ዩኒቨርሲቲያችን የ2010 ዓ.ም የትምህርት ዘመንን በሰላም እና በከፍተኛ ስኬት በማጠናቀቁ  የዩኒቨርሲቲያችን ቤተሰቦች እና ወዳጆች እንኳን ደስ አላችሁ!

ለዚህ ስኬት እንድንበቃ የበኩላችሁን አሻራ ያኖራችሁ ውድ የነገ ተስፋዎች ተማሪዎቻችን፣ ከትምህርታዊ እውቀት በላይ የሆነ የህይወት ስንቅ አስታጣቂ መምህራኖቻችን፣ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትሉ በፍፁም የሀላፊነት ስሜት ዩኒቨርስቲያችሁን ያገለገላችሁ የአስተዳደር ሰራተኞች፣ ዩኒቨርሲቲያችንን ጥልቅ በሆነ የባለቤትነት ስሜት በስስት አይን እያያችሁ ከጥፋት የጠበቃችሁና ለእድገቱ የበኩላችሁን የሰነዘራችሁ የአካባቢው ነዋሪዎች፣ ውሳኔዎቻችንን በማመን ሀላፊነታችንን በሙሉ አቅማችን እንድንጠቀም ብርታት የሆናችሁን የቦርድ አመራሮቻችን፣ ባሳለፍናቸው ፈታኝ ጊዜያት ሁሉ የተማሪዎቻችንን ደህንነት ለመጠበቅ መላው የግቢው ሰራተኛ ዘብ እየዋለ ሲያድር ውድ የሆነ የግል የጥናት ጊዜያችሁን በመሰዋት ከጎናችን ሳትለዩ በከፍተኛ ጥንካሬ አብራችሁን እየዋላችሁና እያደራችሁ የተማሪዎቻችንን ደህንነት በስኬት ያረጋገጣችሁ፣ ተማሪዎችንን በማስተባበር ግቢያችን ያደመቃችሁ የተማሪዎች ህብረትና የሰላም ፎረም አባላት፣ እርዳታችሁን በፈለግን ጊዜ ሁሉ ፈጥናችሁ የደረሳችሁልን የጉራጌ ዞን አመራር አካላት፤ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር፤ የጉራጌ ዞን ፖሊስ አመራር አካላት፤ የጉራጌ ዞን መብራት ሀይል ቅርንጫፍ ፅ/ቤት፤ የኢትዮጵያ መድህን ድርጅት ወልቂጤ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት፣ የጆካ ሆቴል፣ የብሳቢ ሆቴል፣ የቸሀ ወረዳ አስተዳደር፣ ዮሀንስ ሀይሌ ኮንስትራክሽን፣ የወልቂጤ ኤፍ ኤም 89.2፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወልቂጤ ቅርንጫፍ፣ የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት፣ የጉራጌ ዞን ባህል እና ቱሪዝም ፅ/ቤት፣ ህዝቡን ፍቅር እና ሰላም ለማስተማር ደከመኝ ያላላችሁ የሁሉም እምነቶች አባቶች፣ በዙሪያችን ያላችሁ የቢዝነስ ድርጅቶች እና ሌሎች ያልጠቀስናችሁ አጋሮቻችን እጅግ የከበረ፤ በፍቅር የተዋጀ ምስጋናችን ይድረሳችሁ፡፡

ለትብብራችሁ ከፍ ያለ ምስጋና እናቀርባለን!

የ2010 ዓ.ም ፍሬዎቻችንን የምናስመርቀው ቅዳሜ ሰኔ 30/2010 ዓ.ም ስለሆነ ውድ የዩኒቨርሲቲያችን ቤተሰቦች እባካችሁ ልጆቻችንን የሀገር ዋልታ እና ማገር ያድርጋችሁ በሉልን!!!

ውድ ተመራቂዎቻችን እንኳን ለዚህች ልዩ ቀን አደረሳችሁ!

ልብ በሉ ይህ ቀን የመጀመሪያው መጨረሻ ነው፡፡

ደጀኔ አየለ (ፕ/ር)

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት

Copyright © 2018. Wolkite University. Designed by Wolkite University ICT

Login Form

Register