• Registration

ወልቂጤ ዩኒቨርስቲ በአሜሪካ ሃገር ከሚገኘው ቨርጂኒያ ስቴት አዋርድድ ኮሌጅ ጋር በመተባበር በባዮ ጋዝ አመራረት ዙርያ ለዩኒቨርስቲው እና ለአካባቢው ማህበረሰብ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ የኢንዱስትሪ ትስስር ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ሀይለማርያም እንደገለጹት ዩኒቨርስቲው የማህበረስቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግርየሚፈቱ የተለያዩ የምርምር ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡

አቶ ተስፋዬ አክለውም ዩኒቨርሲቲው በአሜሪካ ሃገር ከሚገኘው ቨርጂኒያ ስቴት አዋርድድ ኮሌጅ ጋር በመተባበር በባዮ ጋዝ አመራረት ዙርያ ለዩኒቨርስቲው እና ለአካባቢው ማህበረሰብ የአቅም ግንባታ ስልጠና በሠጠበት ወቅት ህብረተሰቡ የሚጠቀምበት ባህላዊ የባዮ ጋዝ አመራረት ቴክኖሎጂ የህብረተሰቡ ጉልበትና ገንዘብ ቆጣቢ እንዳልነበረና አብዛኛው የህብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚ ያደረገ እንዳልሆነ ገልጸው አዲሱ ቴክኖሎጂ ዘመናዊና በቀላሉ ከቦታ ወደ ቦታ ማንቀሳቀስ የሚቻልና የተሻለጠቀሜታ እንደሚሰጥም ተናግረዋል፡፡

አዲሱ የባዮ ጋዝ ምርት አዘገጃጀትና አመራረት ቴክኖሎጂ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ዩኒቨርስቲው ከጉራጌ ዞን ውሀ ፣ማእድንና ኢነርጂ ልማት መምሪያ ጋር በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባም ዳይሬክተሩ አመላክተዋል፡፡

ዘገባው የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ነው!!

Copyright © 2019. Wolkite University. Designed by Wolkite University ICT

Login Form

Register