• Registration

 

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር ልማትና ኮርፖሬት ማኔጅመንት ምክትል ፕሬዚዳንት /ቤት በዩኒቨርሲቲው የመንግስት ሠራተኞች አስተዳደር፣ የፋይናንስ አመራርና የግዢ ስርዓትና አፈፃፀም ውጤታማነት ለማሻሻል የሚያስችል ስልጠና ሰጥቷል፡፡

ስልጠናው ከሚመለከታቸው የፌደራል ተቋማት በተጋበዙት ፕሮፌሽናል አሰልጣኞች የተሰጠ ሲሆን በመንግስት ሠራተኞች አስተዳደር፣ በፋይናንስ ስራ አመራር እና በግዢ ስርዓትና ንብረት አስተዳደር ላይ ያተኮሩ ሶስት ሰነዶች በዩኒቨርሲቲው ካለው ነባራዊ ሁኔታ ጋር ተዛማጅነት ባለው ሁኔታ ቀርበው ግልፅና አሳታፊ በሆነ መልኩ ጥልቅ ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡

በስልጠናው የተሳተፉ አካላትም ስልጠናው የአመራሩን ግንዛቤ በማሳደግ እና እርስ በርስ በመተራረምና በመደጋገፍ ቀደም ሲል በአፈፃፀም ሂደት ላይ ይስተዋሉ የነበሩ ክፍተቶችን ለማስተካከልና በቀጣይ የሚኖረው የአሰራር ስርዓትን ለማሻሻል የላቀ ሚና እንዳለው ተናግረዋል፡፡

በስልጠናውም የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዚዳንቶች፣ የሁሉም ኮሌጅ ዲኖች፣ የየትምህርት ክፍሉ ሃላፊዎች እና ዳይሬክተሮች እንዲሁም ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

Copyright © 2020. Wolkite University. Designed by Wolkite University ICT

Login Form

Register