• Registration

ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ ዲግሪ በግል መማር የሚፈልጉ አመልካቾችን ከነሀሴ 13/2011 ዓ/ም እስከ መስከረም 09/2012 ዓ/ም ሲመዘግብ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ ነገርግን በ2011 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ምክንያት ዩኒቨርሲቲ ያልተመደቡና የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ያወጣውን መስፈርት የሚያሟሉ ተማሪዎች የውጤት ሠርተፊኬት በመዘግየቱ ምክንያት ቀርበው መመዝገብ አልቻልንም በማለት ጽ/ቤታችን በመቅረብ ጥያቄ ሲያቀርቡ ቆይተዋል፡፡ በመሆኑም መስፈርቱን የምታሟሉ የዘንድሮ ተፈታኞች ብቻ ከመስከረም 29 እስከ 30/2012 ዓ/ም የ8ኛ ክፍል፣ 10ኛ እና 12ኛ ክፍል ሠርተፍኬትና ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪበት ዋናውና ሁለት ፎቶኮፒ በመያዝ ባሉን የትምህርት መስኮች ሪጅስትራር ዳይ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 02 በአካል በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

ማሳሰቢያ፡-

  • መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾች የመግቢያ ፈተና የሚሰጠው ጥቅምት 06/2012 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 በየትምህርት ክፍሉ መሆኑን አውቃችሁ ከወዲሁ በመዘጋጀት በዕለቱ ማንነታችሁ የሚገልጽ መታወቂያ ይዞ መምጣት ይጠበቅባችኋል፡፡

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሪጅስትራር ዳይ/ጽ/ቤት!!

Copyright © 2019. Wolkite University. Designed by Wolkite University ICT

Login Form

Register