2009 ዓ.ም የኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ቀን ከግንቦት 19-20/2009 ዓ.ም በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በደማቅ ሁኔታ ይከበራል፡፡

2009 ዓ.ም የኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ቀን ከግንቦት 19-20/2009 ዓ.ም በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በደማቅ ሁኔታ ይከበራል፡፡

በዚህ ሃገራዊ ክብረ-በዓል ልዩ የፈጠራ ውድድር፣ አውደ-ርዕይ፣ ስፖርታዊ ውድድሮች፣ የፓናል ውይይት፣ የዩኒቨርሲቲ ጉብኝት፣ የደም ልገሳ፣ የሙዚቃ ኮንሰርትና ልዩ የፊልም ምርቃት ይካሄዳል፡፡

በክብረ-በዓሉ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሣለኝ፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ የትምህርት ሚኒስቴር፣ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካዮች እንዲሁም በሀገሪቱ የሚገኙ የ44ቱ ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎች ህብረት ተወካዮች፣ ፕሬዝዳንቶችና ተጋባዥ እንግዶች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል፡፡