የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ በዛሬው ዕለት መደበኛ ስብሰባውን ያደረገ ሲሆን በዚሁ መደበኛ ስብሰባው ላይ የዩኒቨርሲቲውን የዘጠኝ ወር እቅድ አፈጻጸም እና የግንባታ ፕሮጀክቶች ዕቅድ አፈጻጸምን በዝርዝር ገምግሟል፡፡
ከዚህም ባሻገር በመገንባት ላይ የሚገኘውን የአስተዳደር ኮምፕሌክስ ሕንጻ እንዲሁም በጉብሬ ከተማ በመገንባት ላይ ያለውን የማህበረሰብ ትምህርት ቤትን ጎብኝቷል፡፡ በመጨረሻም የስራ አመራር ቦርድ አባላቱ የችግኝ ተከላ ያካሄዱ ሲሆን በቅርቡ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ያገኙትን ፕሮፌሰር ካሳሁን ተስፋዬ እንኳን ደስ ያልዎት በማለት የስራ አመራር ቦርድ አባላቱ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡
ለጥበብ እንተጋለን !
We Strive for Wisdom!
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት