• Registration

ለፍቅርተ ሀ/የሱስ ውሃ ነክ ስራዎች ጠቅላላ ተቋራጭ
ሀዋሳ

ጉዳዩ፡- ጥሪ ስለማድረግ በተመለከተ

ዩኒቨርሲቲያችን በማህበረሰብ አቀፍ ፕሮግራም፤ በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ የሚያስገነባውን የመጌቻ አነስተኛ መስኖ ልማት ግንባታ ለማከናወን ከተቋማችሁ ጋር ውል ገብቶ ድርጅታችሁም ስራውን ተረክቦ እያከናወነ እንደነበር ይታወቃል፡፡

 

ሆኖም የግንባታው ስራ ለረጅም ቀናት ተቋርጦ መቆየቱ የግንባታው አማካሪ ድርጅት ካቀረበው ሪፖርትና ካደረግነው የሳይት ምልከታ ለመገንዘብ ችለናል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በግንታው ሒደት ውስጥ የተለዩ ተጨማሪ ስራዎች መኖራቸው ለተቋማችን አሳውቃችሁት በነብውና  በሙያኞቻችን ተጠንቶ በተረጋገጠው መሰረት ተጨማሪ ስራዎችን በመለየት ለተቋማችሁ ለማቅረብ እንዲሁም ስራው መቀጠል ስለሚኖርበት ሁኔታ ለመነጋገር በስልክ እና በተለያዩ አማራጮች ድርጅታችሁን ለማግኘት ያደረግነው ሰፊ ጥረት ከድርጅታችሁ በኩል ማንንም ማግኘት ባለመቻላችን ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ 

ከዚህም በተጨማሪ ፕሮጀክቱ ከማህበረሰቡ የዕለት ተዕለት ኑሮ ጋር እጅግ የተሳሰረ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የፕሮጀክቱ የመጨረሻ ተጠቃሚ የሆነው ማህበረሰብ በፕሮጀክቱ መጓተት ምክንያት ሊያገኘው ይገባ የነበረ ጥቅም ከማጣቱም በተጨማሪ በመንግስት መዋቅር ላይ የመልካም አስተዳር ጥያቄን ፈጥሯል፡፡ 

ስለሆነም አማካሪያችን በሰጠን ምክረ ሀሳብ መሰረት ድርጅታችሁ የችግሩን ጥልቀትና አሳሳቢነት ተገንዝቦ እስከ 21/01/2013 ዓ.ም ድረስ ወደ ስራ በመመለስ እና ይህንኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ በጽሁፍ ወልቂጤ ዪኒቨርሲቲ ፕሮጀክት ጽ/ቤት እንድታሳውቁ እየጠየቅን፤ ይህ ሳይሆን ቢቀር ተቋማችን ለፕሮጀክቱ ቀጣይነት ሲል በውለታው መሰረት አስፈላጊውን ህጋዊ አግባብ ተከትሎ ወደ ቀጣይ እርምጃዎች ለመሄድ የሚገደድ መሆኑ አሳውቃለሁ፡፡  

‹‹ከሠላምታ ጋር››

ግልባጭ

  • ለፕሬዝዳንት ጽ/ቤት                                                                                                                                                                  ተስፋሁን ገብሩ
  • ለቢ/ል/መ/አስ/ ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት
  • ለቢይቦኒ አማ/ኃ/የተ/የግ/ማ
  • ለህግ ዳይሬክቶሬት
  • ለግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት

ወልቂጤ ዩኒቨረሲቲ

Copyright © 2020. Wolkite University. Designed by Wolkite University ICT

Login Form

Register