01/02/2014 ዓ.ም
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ነሐሴ 29/ 2013 ዓ.ም በመደበኛው ፕሮግራም በመጀመሪያ ድግሪ ካስመረቃቸው አዲስ ምሩቃን መካከል በአጠቃላይ ውጤታቸው (CGPA) ብልጫ ውጤት ይዘው የተመረቁትን በመምህርነት ሙያ ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሠረት በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ነሐሴ 29/ 2013 ዓ.ም በመደበኛው ፕሮግራም በመጀመሪያ ድግሪ ለተመረቃችሁና በዩኒቨርሲቲው በመምህርነት ሙያ ተቀጥራችሁ ማገልገል ለምትፈልጉ፤
- ለወንድ ምሩቃን ከተመረቃችሁበት ኮሌጅ ብልጫ ውጤት በማምጣት ከኮሌጅ ከ 1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃን በመያዝ የሜዳሊያ ተሸላሚ የነበራችሁ፣
- ለሴት ምሩቃን ከተመረቃችሁበት ት/ክፍል ከ 1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃን በመያዝ በብልጫ ውጤት የተመረቃችሁ፡፡
በዩኒቨርሲቲው የሰው ኃብት ልማትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ጽ/ቤት የት/ት ማስረጃችሁን ይዛችሁ በአካል በመቅረብ ከ 01/02/2014 እስከ 05/02/2014 ዓ.ም ባሉት 5 ተከታታ የሥራ ቀናት ውስጥ ብቻ እንድትመዘገቡ እያሳሰብን የቅጥር ፈተናው በቀን 08/02/2014 እና በቀን 09/02/2014 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑንም ጭምር ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡
ማሳሰቢያ፡ የቅጥር ፈተናው ከሰለጠናችሁብት ሙያ ጋር የሚያያዝ፣ አጠቃላይ የእንግሊዘኛ ቋንቋ እንዲሁም የሥነ-ምግባር ጉዳዮችን ያካትታል፡፡