ርእይ

  • በ2022 ዓ.ም በኢትዮጵያ ከሚገኙ ተግባራዊ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ቀዳሚ ሆኖ መገኘት!

ተልዕኮ

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እንደ አንድ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም በሀገራዊ የትኩረት አቅጣጫ መሠረት ፈጣንና ዘላቂ እድገት ማምጣት የሚችል ጥራት ያለው ትምህርት በመስጠት ዲሞክራሲያዊ ባህልን የተላበሰና ኃላፊነት የሚሰማው ዜጋ ማፍራት ፤ ችግር ፈቺ ምርምር በማካሔድና የቴክኖሎጂ ሽግግርን በማዳረስ የህብረተሰቡን የኑሮ ደረጃ ከፍ ማድረግ ፤ የለውጥ መሣሪያዎችን ተግባራዊ በማድረግ ፣ የተቋሙ አቅም ግንባታ በማሳደግና መልካም አስተዳደርን በማስፈን ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት የመስጠት ተልዕኮን አንግቦ የተነሳ ነው፡፡

በዚህ መሠረት፡-

  • በመካከለኛና በረጅም ጊዜ የሀገሪቱ ልማት የሚፈልገውን በዕውቀት የበለፀጉ ፣ በሙያቸው ክህሎት የጨበጡ ፣ በአመለካከታቸው የተቃኙና የዜግነት ግዴታቸውን በመወጣት አገራቸውንና ራሳቸውን ተወዳዳሪ የሚያደርጉ ምሩቃንን ማፍራት፤

  • በሀገራዊ እድገት ላይ ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱና የተለየ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ መስኮች በተለይም የልማት ድርጅቶችንና ተቋማትን እንዲሁም በኢንዱስትሪው ልማት መስክ ልማቱን ለማቀላጠፍ የሚረዱ እውቀትንና የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ውጤቶችን ማቅረብ፤

  • በተለይ በክልሉና በአካባቢው ከሚካሄዱ እንቅስቃሴዎች ጋር በተያያዘ የማኅበረሰብ አገልግሎት በመስጠት ልማታዊ ሚና መጫወት።

እሴቶች

  • እውነትን የመሻት እና ሐሳብን በነጻነት መግለጽ

  • ተቋማዊ ተወዳዳሪነት እና ትብብር

  • በተልዕኮ ስኬት ላይ የተመሠረተ ታዋቂነት

  • ተቋማዊ ነጻነትን ከተጠያቂነት ጋር ማረጋገጥ

  • ሙስናን መጸየፍ እና መታገል

  • ሕጋዊነት እና ፍትሐዊነት

  • ውጤታማ የሀብት አጠቃቀም

  • ቀልጣፋ እና ጥራት ያለው አገልግሎት

  • አሳታፊነት

  • ብዝሃነትን መጠበቅ

  • እውቅና መስጠት እና ፈጠራን ማበረታታት

መሪ ቃል

  • ለጥበብ እንተጋለን!
Copyright © 2024. Wolkite University. Designed by Wolkite University ICT