በተማሪዎች ህብረት ስራ አስፈፃሚ (ዘርፎች) የሚከናወኑ ተግባራት

  1. አካዳሚክ ዘርፍ
  • የየኮሌጁን አካዳሚክ ተጠሪዎች (የዲፓርትመንት እና ኮሌጅ ኮሚቴ)መከታተልና ተጠናክረው እንዲሰሩ ማድረግ፣
  • በተማሪዎች መካከል ችግር ፈቺ የጥናታዊ ፅሁፎችና ፈጠራ ሥራዎች ውድድር ማካሄድ፣
  • በትምህርት መርሀ ግብሩ በፈቃደኝነት አገልግሎት የሠጡ ተማሪዎችን በሥራቸው እውቅና እንዲያገኙ ማድረግ፣
  • የመማር ማስተማሩ ሂደት በአግባቡ መካሄዱን ይከታተላል
  • ተማሪዎች በት/ት ጉዳይ የሚገጥሟቸውን ችግሮች አብሮ ይፈታል
  1.  የመረጃና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ
  • አጠቃላይ የህብረቱን እንቅስቃሴ ለተማሪዎች በተለያዩ መንገዶች ማሳወቅ
  • የተለያዩ ክበረ በአላት እና የተማሪዎች ባእላትን ያዘጋጃል
  • ህብረቱን ከ ዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት አካላት ጋር እና ከተማሪው ጋር ጥብቅ ግንኙነት እንዲኖረው ማድረግ
  • ልዩ የፓናል ውይይት ያዘጋጃል እንግዶችንም ይጋብዛል
  • ህብረቱ ዓመታዊ መጽሔት እንዲኖረው ማድረግ፣
  • የተለያዩ የኪነ ጥበባት መድረኮችን ማዘጋጀት፣
  1. የጠቅላላ አገልግሎት ዘርፍ
  • አጠቃላይ የተማሪዎች አገልግሎቶቸን መከታተል እንደ አስፈላጊነቱ ሀሳቦችን መጠቆም
  • የተማሪ መገልገያ ቁሳቁሶች እንደአስፈላጊነቱ እንዲጠገኑ ከሚመለከተው አካል ጋር መስራት፣
  • ልብስ ንጽህና ሊሰጡ የሚችሉ አካላትን ማስገባት፣
  • በየህንጻው ያሉ መጸዳጃ ቤቶችና መታጠቢያዎች ስራ እንዲጀምሩ ሁኔታዎችን ማመቻቸት፣
  1. የዲሲፕሊን ጉዳዮች ዘርፍ
  • ተማሪውን በሚመለከቱ የዲስፕሊን ጉዳዮች ላይ ተሳታፊ ይሆናል
  • ተቀዋሙ የሚያወጣውን የተማሪዎች መተዳደሪያ ደንብ ለተማሪው ያሳውቃል
  • በተለያዩ የዲሲፕሊን ጉዳዮች ላይ ከተማሪዎችና ከጠቅላላው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ጋር አብሮ መስራት፣
  • ዲሲፕሊን ጥፋት ለሚፈፅሙ ተማሪዎች የተቋሙ ሰራተኞች በቂ መረጃ በማጠናቀር ከጥፋታቸው እንዲማሩ ማድረግና አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ፣
  1. የምግብ ዘርፍ
  • ምግብ ሜኑ አቅርቦት ግዢ በተመለከቴ ከሚመለከተው ክፍል ጋር በመሆን በሂደቱ ይሳተፋል
  • የምግብ ሜኑ በተማሪዎች ፍላጎት እና በጀት መጠን መሰራቱን ከሚመለከተው ጋር በመሆን ያረጋግጣል፤
  • የሚቀርበው ምግብ፤ጥራት እቃዎች ንጽህና በአግባቡ መሆኑን በየቀኑ ያረጋግጣል
  • ከምግብ ጋር ለሚፈጠሩ ችግሮች ከሚመለከተው ክፍል ጋር አፋጣኝ መፍትሄ ይፈልጋል
  • ለተማሪዎች የተመደበ በጀት በአግባቡ ስራ ላይ መዋሉን አግባብነት ካለው አካል ጋር በመሆን ይቆጣጠራል፤
  1. .ስፖርትና መዝናኛ ዘርፍ
  • በዲፓረትመንት እና በኮሌጆች ተማሪዎች መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያጠናክሩ ስፖርታዊ ውድድሮቸን ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን ያዘጋጃል
  • በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የተለያዩ የስፖርት እና የመዝናኛ ፌስቲቫሎቸ እንዲዘጋጁ ያደርጋል
  • አስፈላጊ የሆኑ የስፖርት እና የመዝናኛ ቦታዎች ያመቻቻል
  • ተማሪዎች የመዝናኛ አገልግሎት እንዲያገኙ አመቺ ሁኔታዎችን ይፈጥራል
  • ተማሪዎች በተለያዩ ስፖርቶች እንዲሳተፉ ያበረታታል
  1. .የበጎ አድራጎት ዘርፍ
  • በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የኢኮኖሚ ችግር ያለባቸውን ተማሪዎች ተጨባጭ ሁኔታ አጥንቶ የሚደገፉበትን መንገድ ያመቻቻል፡፡
  • ተማሪዎች በቋሚነት ሊረዱ የሚችሉ አገልግሎቶችን ይሰጣል፣
  1. የሴቶች ጉዳይ ዘርፍ
  • በህገ መንግስቱ የተደነገጉ የሴቶች መብቶች እንደተጠበቁ ሆኖ ሴት ተማሪዎች መሰረታዊ መብቶች መከበራቸውን ይከታተላል ያስከብራል
  • ሴት ተማሪዎች የሚደርስባቸውን የአካል እና የስነ-ልቦና ጥቃት በማጥናት ይከላከላል፤ የምክር አገልግሎት የሚያገኙበትን ሁኔታ ያመቻቻል
  • ሴት ተማሪዎች በትምህርታቸው ውጠየታማ እንዲሆኑ ለማድረግ ልዩልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን በመለየት ድጋፍ እንዲያገኙ ያደርጋል
  • በውጤታቸው ደከም ያሉ ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት እንዲገኙ ማድረግ፣
  • አዲስ ተመድበው ለሚመጡ ሴት ተማሪዎች አቀባበል ማድረግና በነባር ሴት ተማሪዎችና መምህራን ትምህርት ማሰጠት፣
  1. የአካል ጉዳተኞች ዘርፍ
  • የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች መከበራቸውን ያረጋግጣል
  • በዶርሚተሪ፤ካፍቴሪያ፤በክሊኒክ፤በላይብረሪና በሌሎችም አገልግሎት አካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን ልዩ ድጋፍ ማግኘታቸውን ያረጋግጣል
  • አካል ጉዳተኞችን በማሰባሰብ ልዩ ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረግ፣
  • በተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች እንዲሳተፉ ያደርጋል፣
  1. .የፋይናንስ ጉዳዮች ተጠሪ
  • የህብረቱን ገቢና ወጪዎች ይቆጣጠራል
  • የህብረቱን ሂሳብ በታወቀ የሂሳብ አሰራር መሰረት መንቀሳቀሱን ይቆጣጠራል

   11.ክበባት እና ማህበራት

  • የክበባት እና ማህበራትን መከታተል አዳዲስ ከበቦች እና ማህበራት እንዲኖሩ ድጋፍ ማድረግ
  • ለክበባት እና ማህበራት አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያገኙ ሁኔታዎችን ማመቻቸት
  • የተለያዩ በዩኒቨርሲቲው ብሎም በህብረቱ የሚሰጡትን በአላት በተሳካ ሁኔታ እንዲከበሩ ማድረግ
  • የስነ-ጽሁፍ ምሽት ያዘጋጃል
  • ለክበባት ድጋፍ የሚያደርጉ ድርጅቶችን ያፈላልጋል
Copyright © 2024. Wolkite University. Designed by Wolkite University ICT