የ2015 ዓ.ም ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በፕሮግራም በጀትና ዕቅድ ዳይሬክቶሬት ተዘጋጅቶ የቀረበ ሲሆን በቀረበው ሪፖርት ዙሪያ ከዩኒቨርሲቲው ካውንስል አባላት ልዩ ልዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቀርበው የሚመለከታቸው ዳይሬክተሮች እና ምክትል ፕሬዝዳንቶች ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተውበታል፡፡
ከሪፖርቱ ጎን ለጎን ዶክተር ፋሪስ ደሊል እንደገለጹት በ2015 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ በሁሉም የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና ተፈትነው በተሰጠው የመውጫ ፈተና ዩኒቨርሲቲው ካስፈተናቸው ተማሪዎች ውስጥ 79.76% ማሳለፍ የቻልንበት እንደተቋም የስኬት ዓመት እንደነበር አስታውሰው ለዚህም ውጤት መመዝገብ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ የጋራ ርብርብ ውጤት መሆኑን በመግለጽ ለተመዘገበው አመርቂ ውጤት ዶክተር ፋሪስ ደሊል የዩኒቨርሲቲውን ማህበረሰብ በሙሉ አመስግነዋል፡፡
በመጨረሻም የማጠቃለያ ሃሳብ በዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት በዶክተር ፋሪስ ደሊል አማካይነት ለዩኒቨርሲቲው የካውንስል አባላት ቀርቧል፡፡
ለጥበብ እንተጋለን!
We Strive for Wisdom!
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት