የእንሠት ምርትና ምርታማነትን ለማሻሻል እና የአርሶ አደሩ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ ባለድርሻ አካላት ትኩረት ሰጥተው በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ ተገለፀ፡፡

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ከጉራጌ ዞን እርሻና ተፈጥሮ ሃብት መምሪያ ጋር በመተባበር ‹‹በማህበረሰብ ተኮር የተቀናጀ የእንሠት አጠውልግ በሽታ መከላከል ዙሪያ›› ከባለደርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል፡፡

በምክክር መድረኩ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ሲሳይ ሸዋማረ እንደገለፁት ዩኒቨርሲቲው የእንሠት አጠውልግ በሽታ ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ ለመከላከል እና የእንሠት ምርትና ምርታማነትን የሚጨምሩ የተለያዩ የእንሠት ዝርያዎችን በመለየትና በማፍላት የምርምር ስራ በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡

የጉራጌ ዞን እርሻና ተፈጥሮ ሃብት መምሪያ ሃላፊ አቶ አለምይርጋ ወልደስላሴ በበኩላቸው በእንሠት ምርትና ምርታማነት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ያለው የእንሠት አጠውልግ በሽታን በወቅቱ የመከላከልና የመቆጣጠር ስራ ካልተሰራ በሠብል ምርቱ ላይ ውድመትን ከማድረሱም ባሻገር በማሳው ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደሚያደርስ ገልፀዋል፡፡

የእንሠት አጠውልግ በሽታን በሚገባ ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የእንሠት ሰብል ማምረቻና መገልገያ መሳሪያዎችን በንፅህና መያዝና መጠቀም ዋንኛው ዘዴ እንደሆነ በተለያዩ የምርምር ስራዎች ማረጋገጥ መቻሉን ተገልጿል፡፡

በሽታውን በዘላቂነት ለመከላከል እና የእንሠት ሰብልን ምርትና ምርታማነቱን በማሻሻል አርሶ አደሩ ተጠቃሚ ለማድረግ የምርምር ተቋማት፣ የግብርና ኤክስቴንሽን እና አርሶ አደሩ በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባም በመድረኩ ተመክሮበታል፡፡

‹‹የህዝብ እና አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት››

 

Contact

Tamru Demsis (Ph.D)
Ac/V/President
Wolkite University, 07
Wolkite, 07
Ethiopia
+251 11 3220054
Mobile: 0930289749
This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
Scroll to top