• Registration

 

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በ2011 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወር እቅድ አፈፃፀም ዙሪያ ውይይት አደረገ፡፡

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ደጀኔ አየለ በውይይት መድረኩ ላይ ዩኒቨርሲቲው የተጣለበትን ተልዕኮ ለማሳካት የተሻለ ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልፀው ለውጡ በበለጠ ለማስቀጠልም ሁሉም የተቋሙ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኛ በቅንጅት ትኩረት ሰጥቶ መስራት አለበት ብለዋል፡፡

በውይይት መድረኩ የመማር ማስተማር፣ የአስተዳደር ልማትና ኮርፖሬት ማኔጅመንት፣ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት፣ የቢዝነስ ልማትና መልካም አስተዳደር እና የፕሬዚዳንት ፅ/ቤት የዘጠኝ ወር እቅድ አፈፃፀማቸው ቀርቦ ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን በተቋሙ የስራ እንቅስቃሴ ዙሪያ በሚስተዋሉ ጉድለቶች ከመተቻቸትና ከመወቃቀስ ይልቅ ቀርቦ በመነጋገር፣ እርስ በርስ በመገነባባት እና የመፍትሄ አካል በመሆን ለተቋሙ እድገት ሁሉም በቅንጅት ሊሰራ እንደሚገባ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎችም በእቅድ አስተቃቀድ፣ በበጀት ምደባና አጠቃቀም፣ በግዥ ስርዓት ሂደት፣ በንብረት አያያዝና አጠቃቀም፣ በሠራተኞች ምደባና የስራ ሰዓት አጠቃቀም አንዲሁም በሌሎች ዙሪያ የተለያየ ጥያቄና አስተያየት አቅርበው በመድረኩ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

በውይይቱም የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ የኮሌጅ ዲኖች፣ የየትምህርት ክፍሉ ሃላፊዎች፣ ሁሉም የተቋሙ ዳይሬክተሮች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው አካላት ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

                                  ዘገባው የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ነው!!

Copyright © 2020. Wolkite University. Designed by Wolkite University ICT

Login Form

Register