(ነሀሴ 24/2015ዓ.ም የወ/ዩ/የህ/ዓ/ግ/ዳ/ት) ፡- በጉራጌ ዞን ከሚገኙ ከ8ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ካሉት ተማሪዎች መካከል የተውጣጡና በክረምቱ መርሀ ግብር በሳይንስ ፣ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስናና ሂሳብ ( STEM) ፕሮግራም ላይ በመሳተፍ ላይ የሚገኙት ጎበዝ ተማሪዎች በአብዛኛው በቤተሙከራ የተደገፈ ፣ በተግባራዊ ትምህርት የታገዝ ፣ተማሪዎች ተገቢውን ዕውቀት እና ክህሎት እንዲጨብጡ በማድረግ ረገድ ላይ ትኩረት ያደረገ እና የተማሪዎችን የፈጠራ ችሎታ የሚያዳብር ስልጠና እጅግ በተጠናከረ መልኩ በዩኒቨርሲቲው በመሰጠት ላይ ይገኛል ፡፡
በማዕከሉ የሚሰጠው ስልጠና የፈጠራ ስራን ስለሚያበረታታ ዘመኑን የዋጁና በሳይንስና ቴክኖሎጂ የበቁ ተመራማሪዎችን በማፍራት ረገድ የጎላ ሚና አለው፡፡
ለጥበብ እንተጋለን!
We Strive for Wisdom!
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት