ክፍት የሥራ ቦታ

ማስታወቂያ

National Exit Model Examination Schedule

National Exit Model Examination Schedule of Examinees assigned in Wolkite University. Students who need account activation can go to Central Library starting from tomorrow  morning

Read more ...

ማስታወቂያ

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ለተመደባቹህ የሪሜዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች በሙሉ፣

Read more ...

በ2016 ዓ.ም በሀገር-አቀፍ ደረጃ የተሰጠውን Graduate Admission Test (GAT) የመግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ያለፋችሁ የድህረ ምረቃ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

በ2016 ዓ.ም በሀገር-አቀፍ ደረጃ የተሰጠውን Graduate Admission Test (GAT) መግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ትምህርት ሚኒስቴር በወሰነው መቁረጫ ነጥብ መሰረት ማለፋችሁን ያረጋገጣችሁ

Read more ...
















 

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ከጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ጋር በመተባበር የቅድመ- መደበኛ ትምህርት የጉራጊና መጽሃፍት ትውውቅ የአሰልጣኞች ስልጠና ሰጥቷል፡፡

በዚህም የስልጠና መድረክ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው የምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ዮሃንስ ገብሩ እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው በትምህርት ዘርፉ የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ መሆኑን አስታውሰው ከእነዚህም መካከል በ19 ትምህርት ቤቶች የዩኒቨርሲቲውን መምህራን በመላክ የማጠናከሪያ ትምህርት (ቱቶሪያል) መስጠቱን፣ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት ማበርከቱን እንዲሁም አሁን ላይ በጉብሬ ከተማ ላይ በማስገንባት ላይ ያለው የማህበረሰብ ትምህርት ቤት ዩኒቨርሲቲው እያደረገ ላለው ድጋፍ ዋነኛ ማሳያ ነው በማለት ገልጸዋል፡፡

ዶክተር ዮሀንስ አያይዘውም በጉራጊና ትምህርት ዝግጅት እንቅስቃሴም ዩኒቨርሲቲው ከፊደል ቀረጻ ጀምሮ የተለያዩ ድጋፎችን ማድረጉን አብራርተዋል፡፡ ም/ፕሬዝዳንቱ አያይዘውም በጉራጊና ቋንቋ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ስልጠና ላይ የተሳተፉት ሰልጣኝ መምህራኖች ተገቢውን እውቀት በመቅሰም የመማር ማስተማር ሂደቱን እንዲያከናውኑ አሳስበዋል፡፡

የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ሃላፊ አቶ መብራቴ ወልደማርያም በበኩላቸው የጉራጊና ቋንቋ በተለያዩ ምክኒያቶች ወደ ስርዓተ-ትምህርት ትግበራ ሳይገባ መቆየቱን ገልጸው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በተደረጉ ሁለንተናዊ ጥረቶች በ2013 ዓ.ም የጉራጊና የፊደል ገበታ የማስጠናት ስራዎች መጀመሩን ጠቅሰው በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የቅድመ መደበኛ ትምህርት የመጽሃፍት ዝግጅት መደረጉንና በ2015ዓ.ም የትምህርት ዘመን በ20 ትምህርት ቤቶች የሙከራ ትምህርት ሲሰጥ መቆየቱን አብራርተዋል፡፡

አቶ መብራቴ አያይዘውም ከዛሬው የጉራጊና ቋንቋ የቅድመ መደበኛ ትምህርት የመጽሃፍ ይዘት ትውውቅ በኋላ በሁሉም የዞኑ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ህዳር 03/2016ዓ.ም ፕሮግራሙ በይፋ ይጀመራል ብለዋል፡፡ በ2016ዓ.ም የትምህርት ዘመንም የአንደኛ ክፍል የጉራጊና ቋንቋ የሙከራ ትምህርት እንደሚሰጥ አሳውቀዋል፡፡

በዞኑ ትምህርት መምሪያ የስርዓተ ትምህርት ክፍል ሃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ገነት ደምስስ በበኩላቸው ህጻናት ትምህርት በሚጀምሩበት በለጋ ዕድሜያቸው በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው መማራቸው ትርጉም ከመፈለግ ይልቅ ቀጥታ ትምህርቱን እንዲገነዘቡት እና እንዲረዱት በማድረጉ የትምህርት ፍላጎታቸው እንዲጨምር እና የወደፊት የትምህርት ርዕይ እንዲሰንቁ ያደርጋቸዋል ብለዋል፡፡ ወ/ሮ ገነት አክለውም ህጻናት በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ሲማሩ ለትምህርት ጥራት ውጤታማነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ገልጸዋል፡፡

በስልጠናውም ላይ ከዞኑ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ መምህራን ፣የትምህርት ቤት ሃላፊዎች እና የተለያዩ የባለድርሻ አካላት ተሳትፈውበታል፡፡

ለጥበብ እንተጋለን!

We Strive for Wisdom!

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

በዓለም አቀፍ የትምህርት ተቋም አማካይነት ለወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሴት ተማሪዎች የአመራርነት ስልጠና መሰጠት ጀመረ

Read more ...

የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ 13ኛ ዓመት አስመልክቶ “ የዓባይ ዘመን ትውልድ “ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ የስነ-ጽሁፍ ፕሮግራም በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ

Read more ...

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የማኔጅመንት አባላት የዋቤ የንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ የፈረዝየ የአቮካዶ እርሻን እና የምርምር ጣቢያ የስራ እንቅስቃሴዎችን ጎበኙ።

Read more ...

በ2016 የትምህርት ዘመን ለማማካሻ ትምህርት (Remedial) ወደ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡት ተማሪዎች በዛሬው ዕለት ወደ ተቋሙ መግባት ጀምረዋል

Read more ...

Public Lecture has been held at Wolkite University

Read more ...

በ2015 ዓ.ም. በመውጫ ፈተና (Exit Exam) ከፍተኛ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ኮሌጆችና የትምህርት ክፍሎች እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው ባለድርሻ አካላት እውቅና ተሰጠ

Read more ...

“የባህር በር ጥያቄ የፖለቲካ ወይስ የህልውና ጥያቄ ? “ በሚል ርዕስ ላይ ያተኮረ ሴሚናር በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ

Read more ...

ዩኒቨርሲቲያችን በአገር አቀፍ ደረጃ በተዘጋጀው የአቪዬሽን ኢኖቬሽን ኤክስፖ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል

Read more ...

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እያከናወነ ያለውን ተስፋ ሰጪ ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት የትምህርት ሚኒስቴር የሱፐርቪዢን ቡድን አሳሰበ

Read more ...

Announcement for Test Takers of National Graduate Admission Test (GAT)

Read more ...

የ2015 ዓ.ም በጀት ዓመት የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮጀክቶች በዩኒቨርሲቲ ደረጃ በመገምገም ላይ ይገኛሉ

Read more ...

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ውስጥ የሚገኘው የጨቅላ ሕጻናት የእንክብካቤ ማዕከል እና የመምህራን መኖሪያ በሆነው አፓርታማ ግቢ ውስጥ የሚገኘው ሞዴል የማህበረሰብ መድሃኒት ቤት በይፋ ተመረቁ

Read more ...

በ2014 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብርን ለመተግበር በዋቤ ችግኝ ጣቢያ የተዘጋጁት ችግኞችን አስመልክቶ የመስክ ጉብኝት ተካሄደ

Read more ...

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ከጉራጌ ዞን ወጣቶች እና ስፖርት መምሪያ ጋር በመተባበር የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ጀመረ፡፡

Read more ...

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሁለት የስፔሻሊቲ የትምህርት ፕሮግራሞችን መስጠት ጀመረ

Read more ...

We have 357 guests and no members online

Wolkite University, P.O.Box 07, Wolkite, Guragie Zone, SNNPR, Ethiopia | +251-113-220042 | pird@wku.edu.et/president@wku.edu.et

Copyright © 2024. Wolkite University. Designed by Wolkite University ICT