• Registration

 

እንደ ሱፐርቪዥን ቡድኑ ገለጻ የሳይንስና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ተማሪዎችን መልሶ በመቀበል የተቋረጠውን ትምህርት ለማስቀጠል አዘጋጅቶ ተደራሽ ባደረገው የብቃት መለኪያ መስፈርቶች መሠረት ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን መልሶ ለመቀበል ከተጠበቀው በላይ የሆነ ዝግጅት አድርጓል፡፡ የሱፐርቪዥን ቡድኑ ለሁለት ቀናት ባካሄደው ውይይትና ምልከታ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እጩ ተማሪዎቹን ተቀብሎ ለማስተማር በሁሉም መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ ያደረጋቸው ዝግጅቶች የኮቪድ-19ን ፕሮቶኮል ባገናዘበ መልኩ የተደራጁ መሆናቸውን አስረድቷል፡፡

እንደ ሱፐርቪዥን ቡድኑ ገለጻ የዩኒቨርሲቲው ሆስፒታል በሁለንተናዊ መልኩ ራሱን ችሎ የተቋቋመ እንደመሆኑ መጠን ኮቪድ-19ን ለመቆጣጠር መሠረታዊ የሆኑትን ተጠርጣሪዎች ለየቶ ማቆያ፣ የህክምናና የማገገሚያ ማዕከላት በተሟላ ሁኔታ መደራጀታቸውን በምልከታው ለማረጋገጥ ችሏል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ዩኒቨርሲቲው በአሁኑ ወቅት እንደ አገር በተያዘው አቅጣጫ መሠረት ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎቹን ተቀብሎ የመማር-ማስተማር ሂደቱን ለማስቀጠል እንዲቻል ቤተ-ሙከራዎች፣ ቤተ-መጻህፍት፣  ላቦራቶሪዎች፣ የመመገቢያ አዳራሾች፣ የመማሪያ ክፍሎችና የመኖሪያ ቤቶች የኮቪድ-19 ፕሮቶኮልን በጠበቀ መልኩ ተደራጅተዋል፡፡ በአንድ መኖሪያ ክፍል ሁለት ተማሪዎች ብቻ መደልድሉን፣ በመማሪያ ክፍሎች አንድ ጠረጴዛ አንድ ተማሪ ብቻ፣ በቤተ-መጻህፍት አንድ ጠረጴዛ ለሁለት ተማሪዎች ብቻ በመደልደል  ተፈጻሚ የሚደረግበት አቅጣጫ መቀመጡን በምልከታው ማረጋገጡን አመልክቷል፡፡

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርሲቲ ሴኔት የሚመራበት ህጋዊ አሠራር ወረርሽኙን ባገናዘበ መልኩ እንዲከለስ ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች እንደ መስፈርት ከማስተዋወቁ በፊት ቀደም ብሎ ወደ የክለሳ ተግባር ማከናወኑ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያው ተቋም እንደሚያደርገው ገልጸዋል፡፡  የኢንፎረሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂም በአግባቡ መዘርጋቱን፣ የደህንነት ካሜራዎች በተለያዩ ቦታዎች መገጠማቸው ለመማር ማስተማሩ ሂደት መሳካት የጎላ ሚና እንዳለችው ቡድኑ አስረድቷል፡፡ እንዲሁም የኮቪድ-19 ፕሮቶኮልን ባገናዘበ ሁኔታ የተማሪዎች የኮርስ ድልድልና የመምህራን ምደባ መደረጉን፣ ከንኪኪ ነጻ ሆኑ የእጅ መታጠቢያዎች በመማሪያ ክፍሎች፣ በካፍቴሪያዎች፣ በተማሪ መኖሪያ ቤቶችና በመግቢያና መውጫ በሮች አካባቢ ከንኪኪ ነጻ የሆኑ የእጅ መታጠቢያዎች በማመቻቸት የግቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ የተከናወነው ዝግጅት ዩኒቨርሲቲው ሰላማዊ የመማር-ማስተማር ሂደን አስተማማኝ በሆነ መልኩ ለማስቀጠል ያለው ተነሳሽነት የሚገልርና ለሌሎች አቻ ተቋማት አርአያነት ያለው መሆኑን የሱፐርቪዥን ቡድኑ አስረድቷል፡፡

እንዲሁም ቡድኑ በየደረጃው ያለው አመራር እየተናበበ ተቀናጅቶ የሚሰራ መሆኑ፣ የተማሪዎች ህብረት በአግባቡ መደራጀቱ፣ሰላማዊ የመማር-ማስተማር እና ኮቪድ-19ን ለመከላከል የተቋቋመው ግብረ-ሀይል በዕቅድ እየተመራ መሆኑ፣ የቀጣይ አምስት አመታት ስልታዊ ዕቅድና የ2013 መሪ ዕቅድ ቀደም ብሎ ተዘጋጅተውና ተሰንደው ሥራ ላይ መዋላቸው ዩኒቨርሲቲው ለደርሰበት ስኬት ቁልፍ ሚና እንዳላቸው ገልጾአል፡፡ በወረርሽኙ ምክንያት ከመደበኛው ሥራቸው ርቀው የቆዩት የተቋሙ መምህራንና

የአስተዳደር ሠራተኞችም በወቅቱ ጥሪ ተደርጎላቸው በተሟላ ሁኔታ ተሰባስበው ወደ ሥራ መግባታቸው ለተማሪዎች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ግብአቶች ተሟልተው በጥንቃቄ መደራጀታቸውን፣ በወረርሽኙ ዙሪያ ግንዛቤ ለማሳደግ የሚያግዙ ባነሮች፣ ማስታወቂያዎችና ፖስተሮች ተዘጋጅተው በተመረጡ ቦታዎች መለጠፋቸው ወቅታዊ መረጃ ለመስጠት በሚያሰችል መልኩ የተደራጀ ድህረ ገጽ መኖሩን በውይይት፣ በሰነድ ፍተሻና በምልከታ ማረጋገጡን አመልክቷል፡፡  

በመሆኑም ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የዝግጅት ምዕራፍ አፈጻጸም መስፈርት በአግባቡ ጠብቆ እየሰራ መሆኑንና  አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ እጩ ተመራቂ ተማሪዎቹን ተቀብሎ የተቋረጠውን ትምህርት ለማስቀጠል የሚያስችለው በበቂ ሁኔታ የተደራጀ ዝግጅት እንዳለው  በመግለጽ ይህንኑ ለሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ሪፖርት እንደሚያደርግ የሱፐርቪዥን ቡድኑ አስታውቋል፡፡

Copyright © 2020. Wolkite University. Designed by Wolkite University ICT

Login Form

Register