• Registration

 

ሰልጣኞችም ከዞኑ ወዴሻ፣ ጎንቸቤቴ እና ጃቱ ቀበሌዎች የተውጣጡ ሴቶች፣ ወጣቶች እና የግብርና ባለሞያዎች ናቸው ስልጠናውም በዩኒቨርሲቲው ግብርና ኮሌጅ እና የንግድና ምጣኔ ኮሌጅ መምህራን የተሰጠ ሲሆን በደን መጨፍጨፍ ጽንሰ-ሀሳቦች, መንስኤዎች እና ውጤቶች፣ የአካባቢ መራቆት ፤ የአካባቢ ጥበቃ እና ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ አንድምታዎቹ፣ የደን ሀብቶች ተግዳሮቶች እና ኢኮኖሚያዊ እድሎች እንዲሁም የአማራጭ የገቢ ምንጮች የወጪ ጥቅም ትንተና እና አነስተኛ የከብት እርባታ ዘዴ፣አነስተኛ የከብት እርባታ ጤና፣ የአነስተኛ ከብት እሴት ሰንሰለት እንዲሁም አነስተኛ የከብት እርባታ አስተዳደ ላይ ያተኮረ ነው፡፡

የግብርና ኮሌጅ መምህር እና የፕሮጀክቱ አስተባባሪ የሆኑት መምህር ዞማ ከፍያለው እንደገለጹት ስልጠናው በጊቤ ሸለቆ ብሄራዊ ፓርክ ዙሪያ የሚኖሩ ማህበረሰቦች ለገቢ ማግኛ ምንጭ በሚል የሚሰሩት የከሰል ማክሰል ስራ እያስከተለ ያለው ጉዳት ከፍተኛ ነው ሲሉ ጉዳቱን ለመቀነስም ማህበረሰብ ተኮር የፍየል ርቢ ስልጠና በመስጠት እና ወደ ተግባር በማሰማራት የተሻለ የገቢ ምንጭ እንዲኖራቸው በማድረግ የጊቤ ሸለቆ ብሄራዊ ፓርክን ከጉዳት ለመታደግ ያለመ ስልጠና ነው ብለዋል፡፡ መምህርት ዞማ አክለውም ከሶስቱም ቀበሌዎች የተውጣጡ በከሰል ማምረት ስራ የተሰማሩ 20 የስልጠናው ተሳታፊዎችም በአራት ማህበራት የተደራጁ ሲሆን ለእያንድአንዳቸው 5 የርቢ ፍየሎችን በመስጠት የሚጀመር ሲሆን ዩኒቨርሲቲውም ድጋፍ እና ክትትል እንደሚያድግ ተናግረዋል፡፡

በስልጠናውም የደን ሃብት ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ በኢትዮጵያ ምን እንደሚመስል እንዲሁም የደን ሃብት አጠቃቀም ተግዳሮቶች የተመለከቱ ጽሁፎች ቀርበው ሰፋ ያለ ማብራሪያ የተሰጠባቸው ሲሆን ከባለድርሻ አካላት ምን ይጠበቃል የሚል የመነሻ ሃሳብ ቀርቦ ውይይትም ተደርጎባቸዋል፡፡

አብዛኛው የማህበረሰብ ክፍል በግብርና ስራ የሚተዳደር ነው ያሉት ተወያዮቹ በአመት አንድ ጊዜ የሚመረተው ምርት ለአመት የሚበቃ ባለመሆኑ ወደ ከሰል ስራ እንደሚሰባሩ የተናገሩ ሲሆን መንግስት እና ባለድርሻ አካላት በቅንጅት በአመት ሁለት ጊዜ ልናመርት የምንችልበት አልያም ሌላ አማራጭ ስራ ቢያመቻችልን ሲሉ አስተያየት አጥተዋል፡፡

Copyright © 2022. Wolkite University. Designed by Wolkite University ICT

Login Form

Register